የአብክመ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ በባህርዳር ከተማ አካሂዷል፡፡
ምንም እንኳን ተቋሙ የክልል አስፈጻሚ አካላትን ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 300/2017 መሰረት በቅርቡ የተቋቋመ ቢሆንም በሁሉም ዞኖች እና ሪጂዮ ፖሊታንት ከተሞች ሙሉ በሙሉ አደረጃጀቱን መሰረት በማድረግ ወደ ስራ መባቱን ገልጸዋል፡፡በበጀት ዓመቱም ዘመናዊ፣ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለመገንባት የሚያስችል ዘርፈብዙ ስራዎች መሰራታቸውን የሚያመላክቱ ሪፖርቶች ቀርበው ተገምግመዋል፡፡ በሪፖርቱም ሁሉም የኮንስትራክሽን ፐፕሮጀክቶች የተቀመጡ የህግ ማዕቀፎችን መሰረት በማድረግ ብቻ በመፈጸም አሁን ካለባቸው ያልተገደበ በጀት እና ጊዜ ብክነት እንዲወጡ ማድረግ የሚያችል ስራ እየተሰራ ይገኛል ፡፡ባሳለፍነው በጀት ዓመት ሁሉም በክልላችን ተግባራዊ የሚደረጉ ፕሮጀክቶች በአግባቡ የተዘጋጀ እና የጸደቀ ዲዛይን ሳይዙ ወደ ጨረታ ሂደት እንዳይገቡ የሚያስችል አስገዳጅ ህግ መውጣቱንም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ገልጸል፡፡ በግምገማ ማጠቃለያውም
1. ስነምግባር የጎደለው አሰራር
2.የቴክኖሎጂ ክፍተት
3. ደካማ የቁጥጥር ስርዓትን
4. ተለዋዋጭ የኮንስትራክሽን ዋጋ
5.ከፍተኛ የውጭ ጥገኝነት
የኢንዱስሪው ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች መሆናቸውን በመገንዘብ የተለየ ርብርብ ማድረግ የሚገባ መሆኑን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል፡፡ በመጨረሻም
ከሪጂዮ ፖሊታንት ከተሞችም
1.ደብረ ብርሀን ከተማ አስተዳደር ኮን/ተ/ጽ/ቤት 1ኛ
2.ባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ኮን/ተ/ጽ/ቤት 2ኛ
3. ጎንደር ከተማ ከተማ አስተዳደር ኮን/ተ/ጽ/ቤት 3ኛ
ከዞኖች
1.ማዕከላዊ ጎንደር ኮን/ተ/ጽ/ቤት 1ኛ
2.ሰሜን ሽዋ ኮን/ተ/ጽ/ቤት 2ኛ
3.ሰሜን ጎንደር ኮን/ተ/ጽ/ቤት 3ኛ ደረጃ በመውጣት ላስመዘገቡት የላቀ ውጤት ዕውቅና ተሰጥቷል::







Leave a Reply