የአማራ ክልል ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ትውውቅ መድረክ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ም/ዳይሬክተር ባምላኩ ደምሌ
/ኢንጂነር/ በሀገር አቀፍና በክፍለ አህጉር ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ;ጥራትና በጀት እንዲከናወኑ ለማድረግ የተደረገው ጥረት አበረታች መሆኑን በመጥቀስ የሚገነቡ ግንባታዎችም ዘመኑ ያመጣቸውን የኮንስትራክሽን ግብዓት እንዲጠቀሙ የማድረግ ስራም የተሰራ ሲሆን ለ150,000 ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩንም ባምላኩ ደምሌ (ኢንጂነር) ገልጸዋል።
በበጀት አመቱ ከ60,000 በላይ የፕላን ስምምነት;የግንባታ ፈቃድ ተሰጥቷል
በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶች እንደተጠበቁ ሆኖ በሥራ ሂደት ላይ ተግዳሮቶች ማጋጠማቸውን የገለፁት የባለስልጣኑ ዳይሬክተር ከዲዛይን ጥራት ችግር፣ የውልና የመረጃ አያያዝ ጉድለት፣ የግንባታ ግብዓቶች የዋጋ ተለዋዋጭነት ዋና ዋና ችግሮች ናቸው።
በቀጣዩ የ2019 በጀት ዓመት ዲጂታል አሠራሮችን እስከ ታችኛው መዋቅር ማውረድ፣ የቆሙ ፕሮጀክቶችን እንዲጠናቀቁ ማድረግና በተቀናጀ መልኩ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።







Leave a Reply