Amhara Construction Authority (Anrs CA) is a government organization dedicated to regulating, streamlining, and enhancing capacity within Ethiopia’s construction industry. Its mission is to provide regulatory services that foster a competitive industry, ensuring projects are executed timely, within budget, and in accordance with established standards, all while considering environmental and social well-being.

ክልላዊ ርዕይ

በ2022 የአማራ ብሔራዊ ክልል በወሳኝ ዘርፎች ንቅናቄ ለኢኮኖሚ ልማት መመንጠቅ አስተማማኝ መሠረት የጣለ እና የመካከለኛ ገቢ ኢኮኖሚ ባለቤት ሆኖ ማየት፤

ተቋማዊ ርዕይ

በ2022 ተወዳዳሪና ምርታማ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ተገንብቶ ማየት፤

እሴቶች

  1. ያለ ክንፍ መብረር ያለ ሙያ መክበር አይቻልምና በሙያ ብቃት እንክበር፤
  2. መታዘዝ ከመስዋዕትነት ይበልጣልና ምርጫችን አገልጋይነት ነው፤
  3. የሰው ወርቅ አያደምቅምና በራሳችን ባህል እንደምቃለን፤ እንጠበቃለን፤
  4. አበው በህግ አምላክ ብለው እንደተገዙለት እኛም ለህግ እንገዛለን
  5. ከባህር የወጣ ዓሳ ላለመሆን ሕዝባዊ ወገንተኝነትን አጥብቀናል፤
  6. ከመቃብር በላይ ስም ይቆማልና አርበኝነት መለያችን ነው፤
  7. ብልህ የዓመቱን፣ ሞኝ የእለቱን ነውና እንደ ብልሆች ሀብትን በአግባቡ ቆጥበን እንጠቀማለን፤
  8. መልካም ሃሳብ ወንዝ ያሻግራልና ልዕለ ሐሳብ ይገዛናል፤
  9. መድረሻውን ያላወቀ የትም ይገኛልና ትኩረታችን ለግቦቻችን ይሁን ብለናል፤
  10. ልዩነታችን ውበት ነውና ብዝሐነት ተቀብለናል፤
  11. ቋጠሮ መፍታት ከውሉ እንዲሉ ምርምርና ፈጠራን ለችግራችን መፍቻ አድርገናል፤
  12. ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር ነውና ቅንጅታዊ አሠራር እሴታችን ነው፤
  13. አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ በመሆኑ ግልፅነትና ተጠያቂነት እሴታችን ነው፡፡ አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ በመሆኑ ግልፅነትና ተጠያቂነት እሴታችን ነው፡፡